ጎንደር፡ መጋቢት 10/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ስምንተኛው የመላው አማራ ስፖርታዊ ውድድር ራያ አላማጣ፣ ራያ ባላ ወረዳ እና ወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራን ለመጀመሪያ ጊዜ በማሳተፍ በጎንደር ከተማ በመካሄድ ላይ ነው።
የቱባ ባህል እና ቅርስ ባለቤቷ ጎንደር ከተማ ከመላው አማራ የተውጣጡ ከአራት ሺህ በላይ የስፖርት ልዑካንን ተቀብላ በማስተናገድ ላይ ትገኛለች። በውድድሩ መክፈቻ የራያ እግር ኳስ ቡድን ከወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ አቻው ጋር ተገናኝቷል።
በውድድሩ መክፈቻ ላይ የጎንደር ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ባዩ አቡሀይ፣ የአማራ ክልል ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ እርዚቅ ኢሳ እና አምባሳደር መስፍን ቸርነት የኢፌዲሪ ባህል እና ስፖርት ሚኒስትር ዲኤታ በውድድሩ መክፈቻ ላይ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ደማቁን የመላው አማራ ስፖርታዊ ውድድር የመክፈቻ ሥነ ሥርአት አሚኮ በቀጥታ አስላልፏል።
👇👇👇
https://www.youtube.com/live/XP56nDTEr5Q?feature=share
የመክፈቻውን ሥነ ሥርአት የቱሪዝም ባለጸጋዋ ጎንደር ከተማ በስኬት አከናውናለች።
የመላው አማራ ስፖርታዊ ውድድር ለሁለት ሳምንት በጎንደር ይቀጥላል።
ዘጋቢ ፦ እሱባለው ይርጋ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!