ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ የአፍሪካ አትሌቲክስ ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው መመረጣቸውን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታወቀ።

118

ባሕር ዳር: ሚያዝያ 19/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ የአፍሪካ አትሌቲክስን በምክትል ፕሬዚዳንትነት እንዲመሩ ተመረጡ፡፡ በዛምቢያ ሉሳካ ሲካሄድ የቆየው የኮንፌዴሬሽን ኦፍ አፍሪካ አትሌቲክስ ኮንግረስ ዛሬ ተጠናቋል፡፡

ረዳት ኮሚሽነር ደራርቱ ቱሉ የአፍሪካ አትሌቲክስን በምክትል ፕሬዚዳንትነት እንዲመሩ በካውንስሉ በሙሉ ድምፅ መመረጣቸውን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!