“ሠራዊቱ የሚለካው በግዳጅ አፈፃፀሙ እንጂ በብሔሩ አይደለም”-ጀነራል አበባው ታደሰ

0
424

ጥር 12/2014 ዓ.ም (አሚኮ) “የኢትዮጵያ ሠራዊት የሚለካው በስራው ስኬት እና በግዳጅ አፈፃፀሙ እንጂ በብሔሩ አይደለም” ሲሉ የመከላከያ ሠራዊት ምክትል ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀነራል አበባው ታደሰ ገለጹ።

ከዚህ በፊት በነበረው የብሔር ተኮር የሠራዊት ግንባታ ዋጋ የከፈለው ራሱ ሠራዊቱ ነው ያሉት ጀነራል አበባው ከኢቲቪ ጋር በነበራቸው ቆይታ ኢትዮጵያዊነትን የተላበሰ እና በሞያው ብቁ የሆነ ሠራዊት እየተገነባ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

በቅርቡ የተካሄደው ወታደራዊ የማዕረግ እና የሜዳልያ ሽልማት በግዳጅ አፈፃፀም ላይ የተመሰረተ፣ በየደረጃው ላሉ እዞች ማዕረግ የተሰጠበት፣ የሠራዊቱ አመራሮችን የሚመጥን እና የሠራዊቱን ሞራል የገነባ እንደነበር ገልፀዋል።

በመጀመሪያው ምዕራፍ ከአሸባሪው ህወሓት ጋር የተፋለመው የኢትዮጵያ ሠራዊት፤ ከጠላት የሰው ኃይል ቁጥር እና ትጥቅ ያነሰ ነገር ግን ኢትዮጵያዊነትን ስንቁ ያደረገ እንደነበርም ተናግረዋል።

ከአሸባሪው ህወሓት ጋር እየተደረገ ያለው ጦርነት አልተጠናቀቀም ያሉት ጀነራል አበባው ሠራዊቱ የምዕራፍ አንዱን ጦርነት አጠናቅቆ ለቀጣይ ግዳጅ እየተዘጋጀ መሆኑን ገልፀዋል።

አሸባሪው የህወሓት ቡድን አሁንም ትንኮሳውን እንዳላቋረጠም ነው ጀነራሉ የተናገሩት።

አሸባሪው ህወሓት ተቆጣጥሯቸው ከነበሩ አካባቢዎች በማስወጣት የተገኘው ድል ሕዝባዊ ድል ነው ያሉት ጀነራሉ የጠላትን የማድረግ አቅም ያዳከመ እና ከፍተኛ የሰው ኃይል እና የንብረት ኪሳራ ያደረሰ መሆኑንም ገልፀዋል።

በጋሸና፣ ሚሌ እና በመሐል ግንባሮች ፈታኝ ውጊያዎች ተደርጎ እንደነበር የገለፁት ጀነራሉ ሠራዊቱ ከፍተኛ ጀብዱ የሠራባቸው እንደነበሩም ተናግረዋል።

ከፍተኛ የፖለቲካ አመራሩ የወሰደው ቁርጠኝነት የሠራዊቱን ዝግጁነት አቅም ያሳደገ መሆኑንም ኢዜአ ዘግቧል።

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/