ምርጫ ከተካሄደባቸው 440 የምርጫ ክልሎች መካከል 221 የምርጫ ክልሎች ውጤት መለጠፋቸውን ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ፡፡

0
217

ምርጫ ከተካሄደባቸው 440 የምርጫ ክልሎች መካከል 221 የምርጫ ክልሎች ውጤት መለጠፋቸውን ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
አስታወቀ፡፡
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 19/ 2013 ዓ.ም (አሚኮ) ሰኔ 14/2013 ዓ.ም ምርጫ ከተካሄደባቸው 440 ያህል ምርጫ ክልሎች ውስጥ
221 የሚሆኑ የምርጫ ክልሎች ውጤቶቻቸውን መለጠፋቸውን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የኮምንኬሽን አማካሪ ወይዘሪት ሶሊያና ሽመልስ ዛሬ በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት፤
ምርጫ ከተካሄደባቸው 440 የምርጫ ክልሎች መካከል ከ50 በመቶ በላይ የሚሆኑት ጊዜያዊ የምርጫ ውጤቶቻቸውን
ለጥፈዋል፡፡
በመግለጫው እንደተመላከተው፤ በአማራ ክልል 40 ያህል የምርጫ ክልሎች ብቻ ውጤት የለጠፉ ሲሆን፤ ይሄም ከጣቢያዎች
ወደ ክልል በሚደረግ የትራንስፖርት ችግር ምክንያት፤ የምርጫ ጣቢያዎች ለሁለት ቀናት የድምጽ ቆጠራ ማካሄድ እና በሌሎችም
የአሰራር ሂደቶች ምክንያቶች የዘገየ መሆኑ ታውቋል፡፡
በሌላ በኩል በኦሮሚያ 125 የምርጫ ክልሎች ውጤት ለጥፈዋል ያሉት ወይዘሪት ሶሊያና፤ አዲስ አበባ ላይ ገና እየተቆጠረ
እንደሆነና 10 ምርጫ ክልሎች ብቻ ውጤት ማሳወቃቸውን ገልጸዋል፡፡
ይህ ሂደት አንድ ተጨማሪ ቀን ወስደው ምርጫ ያካሄዱትን ጋምቤላ እና ሲዳማ ክልሎችን የማያካትት መሆኑን ጠቅሰው፤ ያም
ሆኖ በጋምቤላ ያሉ የምርጫ ክልሎች የተወካዮች ምክር ቤት ቆጠራን ያጠናቀቁ ሲሆን፤ የክልል ምክር ቤት ድምጽም እየተቆጠረ
መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
እስካሁን ወደ ማዕከል ያስገቡና በትክክል መስፈርቱን አሟልተው የተገኙ ሰባት የምርጫ ክልሎች መኖራቸውንም ገልጸዋል፡፡
ወይዘሪት ሶሊያና በመግለጫቸው፤ በደቡብ ክልል በቁጫ ምርጫ ክልል ሲካሄድ የነበረው ቆጠራ እና የውጤት ድመራ
እንዲቋረጥ መወሰኑን አስታውሰው፤ ይሄም በምርጫ ክልሉ ከፍተኛ ቅሬታ የቀረበ ከመሆኑ ጋር የተያያዘ መሆኑንና ውሳኔውን
ተከትሎም ቁሳቁሶቹ ተሰብስበው እንዲቀመጡ መደረጉን አስታውቀዋል፡፡ ኢፕድ እንደዘገበው
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4mw

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here