ምርጫው በሕዝብ ጨዋነት፣ በፖለቲካ ፓርቲዎች ቅን ተሳትፎና በልዩ ልዩ ተቋማት አጋዥነት በሰላም መጠናቀቁን በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አስታወቀ፡፡

0
91

ምርጫው በሕዝብ ጨዋነት፣ በፖለቲካ ፓርቲዎች ቅን ተሳትፎና በልዩ ልዩ ተቋማት አጋዥነት በሰላም መጠናቀቁን በአማራ ክልል
የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አስታወቀ፡፡
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 19/ 2013 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ክልል የሚንቀሳቀሱና በስድስተኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ የተሳተፉ
የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ዛሬ በባሕር ዳር ከተማ የምክክር መድረክ አካሂዷል።
በምክክር መድረኩ በቅድመ ምርጫ፣ በምርጫው ዕለትና ድህረ ምርጫ ወቅት ያጋጠሙ ችግሮችንና በሁሉም ባለድርሻ አካላት
በኩል የተከናወኑ እንቅስቃሴዎችን በተመለከተ በስፋት ተነስቷል።
ውይይቱ ከተጠናቀቀ በኋላ የጋራ አቋም በተያዘባቸው ነጥቦች ላይ ትኩረቱን ያደረገ መግለጫ በፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር
ቤቱ ተሰጥቷል።
በመግለጫውም በክልሉ በተካሄደው ምርጫ በአንጻራዊነት ሁሉም የፖለቲካ ኀይሎች በነጻነት የተንቀሳቀሱበት እንደነበር
ተነስቷል። በምርጫው ሂደት የተስተዋሉ ችግሮች ቢኖሩም በሕዝብ ጨዋነት፣ በፖለቲካ ፓርቲዎች ቅን ተሳትፎና በልዩ ልዩ
ተቋማት አጋዥነት በሰላም በመጠናቀቁ ምክር ቤቱ የተሰማውን ደስታ ገልጿል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የምርጫውን ውጤት በይፋ እስከሚገልጽ ፓርቲዎች የሚጠብቁ መሆኑን በመግለጽም
የሚሰጠውን ውሳኔ በማክበር ቅሬታዎችን በሕግ አግባብ ብቻ ለመፍታት እንደሚንቀሳቀሱም በመግለጫው ተመላክቷል።
በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በተለይም በአማራ ክልል የሰላም ጉዳይ ላይ ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች በጋራ ለመስራት ስምምነት ላይ
መድረሳቸውንም የጋራ ምክር ቤቱ በመግለጫው አስታውቋል።
በምርጫው ሂደት የተፈጠሩ ክስተቶችን የሚያጠና አምስት አባላት ያሉት ኮሚቴ የተቋቋመ ሲሆን ቀጣይ በሚካሄድ መድረክ
ለሚይዙት ኣቋም መነሻ እንደሚደረግና ትምህርት የሚወሰድበት መሆኑን መግባባት ላይ ተደርሷል።
ዘጋቢ:- ደጀኔ በቀለ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here