ማን ዩናይትድ ሮናልዶን የሚተካ አጥቂ ለማግኘት በጥር ወር ዝውውሩ ጥረት እያደረገ እንደኾነ አሰልጣኙ ቴን ሀግ ተናገሩ፡፡

0
57
ባሕርዳር፡ ታኅሣሥ 18/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የማን ዩናይትድ አሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሃግ በጥር መስኮት ዝውወሩ ክርስቲያኖ ሮናልዶን ለመተካት ማንቸስተር ዩናይትድ “አንድ አጥቂ ማምጣት አለበት” ሲሉ ተናግረዋል።
ሮናልዶ ኦልድ ትራፎርድን ኅዳር ወር ላይ መልቀቁ ይታወሳል፡፡
ዩናይትድ በጥር ወር ዝውውሩ ተተኪ ለማግኘት ጥረት እያደረገ ነው፡፡
ኤሪክ ቴን ሃግ ባለፈው ወር የፖርቹጋሉ ኮከብ ተጫዋች መልቀቅን ተከትሎ የዩናይትድን አጥቂ ለማጠናከር ፍላጎት ማሳየታቸው እየተነገረ ነው።
አሰልጣኙ ጥሩ ተጫዋች ከተገኘ ለማስፈረም ክፍት ነው ነገርግን ከዩናይትድ ወጣት አጥቂዎች አንዱን ቡድኑ ማሳደግ ይችል እንደኾነ እየገመገመ ነው ብለዋል።
አሰልጣኙ ለሪፖርተር እንዳሉት እውነት ነው አጥቂ እንደጠፋ እናውቃለን፣ ስለዚህ አጥቂ ማግኘት እንዳለብን አስባለሁ፣ ግን ትክክለኛው መኾን አለበት። ቡድኑ ችግርን ብቻ ይሰጥሃል።እናም ታውቃለህ እዚህ ማንቸስተር ዩናይትድ ውስጥ መስፈርቱ ከባድ ነው ብለዋል።
በምሥጋናው ብርሃኔ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!