ማኅበረሰቡ በቀሪ ቀናት የያዘውን የጦር መሳሪያ በማስመዝገብ የአካባቢውን ሰላም እንዲጠብቅ የአማራ ክልል ሚሊሻ ጽሕፈት ቤት አሳሰበ።

0
123

ባሕር ዳር፡ ግንቦት 16/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ሚሊሻ ጽሕፈት ቤት የሕዝብ ግንኙነት ኀላፊ ገብሩ ታመነ እንዳሉት የአማራ ክልል መንግስት የሕገወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውርን ለመከታተል እና በሕልውና ዘመቻ ወቅት ሕዝቡ የማረከውን መሳሪያ እንዲታጠቅ የክልሉ መንግሥት የገባውን ቃል መሠረት በማድረግ ምዝገባውን ፈቅዷል።

ይህም ማኅበረሰቡ መሳሪያውን በነጻነት ይዞ የአካባቢውን ሰላምና ደሕንነት እንዲጠብቅ ያግዛል ብለዋል።

መዝገባው በአራት ቀን ውስጥ እንዲካሔድ ክልሉ ቢፈቅድም ወቅቱ የዘር ወቅት መኾኑን ተከትሎ ማኅበረሰቡ ያቀረበውን የይራዘም ጥያቄ በመቀበል የምዝገባ ቀኑ እስከ ግንቦት 17/2014 ዓ.ም እንዲራዘም መደረጉን ገልጸዋል።

ማኅበረሰቡ ይሕንን ተረድቶ ያለውን የጦር መሳሪ በማስመዝገብ መመሪያው የጦር መሳሪያ ይዞ መገኘት ከሚከለክላቸው ቦታዎች ውጭ ይዞ በመንቀሳቀስ ሀብቱን፣ ንብረቱን እና የአካባቢው ሰላም እንዲጠብቅ አሳስበዋል።

በቀጣይም የጦር መሳሪያ አያያዝ፣ አጠቃቀም እና የክህሎት ስልጠናዎች የሚሰጥ ይኾናልብለዋል።

በክልሉ የሚደረገው የጦር መሳሪያ ምዝገባ የመጀመሪያ አለመኾኑን ያነሱት ኀላፊው ዛሬም ባለፉት አመታት ክልሉ እንዳደረገው ለክልሉ
ሕዝብ የገባውን ቃል ለመተግበር የፈቀድው እንደኾነ ገልጸዋል።

ማኅበረሰቡም ትክክለኛውን መረጃ ከትክክለኛ እና ከታማኝ ምንጭ መከታተል እንደሚገባ አሳስበዋል።

ዘጋቢ፦ ዳግማዊ ተሠራ

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ‼
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ ‼
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/