መጪው ምርጫ ነሐሴ 23 ቀን2012ዓ.ም እንዲሆን ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።

0
185

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ቀጣዩን ሀገር አቀፍ ምርጫ በተመለከተ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በአዲስ አበባ እየመከረ ነው፡፡

 

በምክሩ ቦርዱ ከዚህ በፊት በጊዜያዊነት ነሐሴ 10 ቀን 2012 ዓ.ም እንደሚከናወን አስታውቆት የነበረውን የምርጫ ቀን ወደ ነሐሴ 23 ቀን 2012ዓ.ም ማሸጋገሩን አስታውቋል።

በቦርዱ የጊዜ ሰሌዳ መሠረት የምርጫ ክልል ካርታ ይፋ የሚሆነው መጋቢት 01 ቀን ይሆንና የምርጫ ጣቢያዎች ዝርዝር ደግሞ መጋቢት 28 ቀን 2012ዓ.ም ይደረጋል፡፡

የተፎካካሪ ፓርቲዎችና ግለሰቦች የመወዳደሪያ ምልክት ማቅረቢያና መወሰኛ ጊዜ ደግሞ ከሚያዝያ 16-30 ባሉት 15 ቀናት እንደሆነ ተገልጿል፡፡

የቦርዱ የተረጋገጠ የምርጫ ውጤት ማሳወቂያ ጊዜም ከነሐሴ 24 እስከ ጳጉሜን 3/2012ዓ.ም እንደሚሆንም ነው ቦርዱ የገለጸው፡፡

በቀረበው የጊዜ ሠሌዳ ዙሪያ ባለድርሻ አካላት እየተወያዩበት ነው፡፡

ዘጋቢ፡- ጽዮን አበበ -ከአዲስ አበባ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here