መካነሰላም እና ከላላ ከተሞች የኤሌክትሪክ ኃይል አገኙ።

0
124

መካነሰላም እና ከላላ ከተሞች የኤሌክትሪክ ኃይል አገኙ።

ታኅሣሥ 03/2014 ዓ.ም (አሚኮ) መካነሰላም እና ከላላ ከተሞች ተቋርጦባቸው የነበረውን የኤሌክትሪክ ኃይል ማግኘታቸውን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታወቀ፡፡

በአሸባሪው ቡድን የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት የወደመባቸው ከተሞች የኤሌክትሪክ አስተላላፊ መስመሮችንና ምሰሶዎችን በመጠገን የኤሌክትሪክ ኃይል መልሶ እንዲያገኙ እየተደረገ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የአማራ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት በደሴ ዲስትሪክት ሥር የሚገኙትን ደሴ፣ ኮምቦልቻ፣ ከሚሴ፣ ባቲ፣ ማጀቴ፣ ጨፋ ሮቢት፣ አቀስታ፣ መሐል ሳይንት፣ ሳይንት አጅባር፣ መኮይና አልብኮ ከተሞችን እስከ ታኅሣሥ 2/2014 ዓ.ም የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ ያደረገ ሲሆን አሁንም ሌሎች ቀሪ ከተሞችን ለማገኛኘት ጥረቱን አጠናክሮ ቀጥሏል ነው የተባለው፡፡

የከተሞችን ኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎት ሳንመልስ ረፍት የሚባል ነገር የለም በማለት ቆርጠው የተነሱት የደሴ ዲስትሪክት ሠራተኞች ዛሬ የመካነ ሰላም እና ከላላ ከተሞች የሚሰጠውን የመካከለኛና ዝቅተኛ መስመር ጥገና በማጠናቀቅ ከተሞቹ ወራሪው ቡድን ከገባበት ጊዜ ጀምሮ ተቋርጦባቸው የነበረውን የኤሌክትሪክ ኃይል ማግኘታቸውን ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡

#ተነሳ!!
#መሪህን ተከተል!!
#ሀገርህን አድን!!
#ነፃነትህን አትስጥ !!
#አካባቢህን ጠብቅ!!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation