መንግሥት የዜጎችን ደኅንነት የማስጠበቅ ግዴታውን ከመቼውም ጊዜ በላይ ሊወጣ እንደሚገባ የተቀናሽ ሠራዊት አባላት ማኅበር ፕሬዚዳንት አስር አለቃ ደጀኔ ሸዋረጋ ተናገሩ፡፡

0
126

አዲስ አበባ: ሰኔ 16/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የተቀናሽ ሠራዊት አባላት ከሕዝቡና ከመንግሥት የጸጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት የዜጎችን በሰላም ወጥቶ የመግባት ነጻነት እንዲጠበቅ ለመሥራት ዝግጁ መኾናቸውን የተቀናሽ ሠራዊት አባላት ማኅበር ፕሬዚዳንት አስር አለቃ ደጀኔ ሸዋረጋ ገልጸዋል፡፡

ከሰሞኑ በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ወለጋ ዞን ጊምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ በንጹሐን አማራዎች አሸባሪው ኦነግ ሸኔ ጭፍጨፋ ፈጽሟል። ከአሚኮ ጋር ቆይታ ያደረጉት የተቀናሽ ሠራዊት አባላት ማኅበር ፕሬዚዳንት አስር አለቃ ደጀኔ ሸዋረጋ ለዚህ አሰቃቂ ጭፍጨፋ መነሻ ያሉትን ሲያስቀምጡ አጥፊዎቹ አማራ ለሀገረ መንግሥት ምሥረታ የነበረውን ሚና በተሳሳተ ትርክት መረዳታቸው፣ ኢትዮጵያን ለመበተን አማራን ማጥፋት ነው የሚል እኩይ ዓላማቸውን ለማስፈጸም ከታሪካዊ ጠላቶች ጋር ማበራቸውና አሸባሪው ትህነግና ፈረሶቹ አማራን በጠላትነት መፈረጃቸው ነው ይላሉ፡፡ ድርጊቱ ሀገር የማፍረስ ውጥን ያለው ነው ሲሉም ገልጸውታል፡፡

የንጹሐንን ግድያ ኢትዮጵያ እንደ ሀገር እንድትቀጥል የሚፈልጉ ኹሉ ሊያወግዙትና በጋራ ሊከላከሉት ይገባል ብለዋል፡፡

መንግሥት ተቀዳሚ ሥራው የዜጎችን ደኅንነት የመጠበቅ ግዴታ ነውና ባለው ኀይልና መዋቅር ተጠቅሞ ይህን አሰቃቂ ድርጊት ሊያስቆመው ይገባል ነው ያሉት።

እንደተቀናሽ ሠራዊት አባላት ማኅበር ዋጋ የተከፈለላት ሀገር ዛሬም እንድትቀጥል፣ ግድያ እና መፈናቀል እንዲቆም የህይወት መስዋእትነት እስከመክፈል ድረስ ዝግጁ ነን ብለዋል፡፡

ዘጋቢ:- ድልነሳ መንግሥቴ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን‼

ከእኛ ጋር ስለኾኑ እናመሰግናለን‼

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J