መንግሥት የክልሉን ዘላቂ ሰላም የማስጠበቅ ሥራውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል የአማራ ክልል የሰላምና ጸጥታ ቢሮ አስታወቀ፡፡

0
178

ባሕር ዳር፡ ግንቦት 15/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል መንግሥት ዘላቂ ሰላም የማስጠበቅ ሥራውን አጠናክሮ እንደሚቀጥል የክልሉ የሰላምና ጸጥታ ቢሮ አስተወቀ፡፡

ቢሮው የክልሉን ወቅታዊ ኹኔታ አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል።

የአማራ ክልል የሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኀላፊ አቶ ደሳለኝ ጣሰው እንዳሉት በተለያዩ ወንጀሎች የተጠረጠሩ ከ4 ሺህ በላይ ተጠርጣሪዎች በሕግ ቁጥጥር ስር ውለዋል።

ከዚህ ውስጥ ከ40 በላይ የሚኾኑት በፍርድ ቤት ተፈርዶባቸው የነበሩ እንደኾኑ ገልጸዋል፤ 210 በነፍስ ግድያ የተጠረጠሩ መኾናቸውን አቶ ደሳለኝ አብራርተዋል፡፡

አኹን ላይ ሕገ ወጦችን ለመያዝ ከሚደረግ ሥራ ውጭ ክልሉ አስተማማኝ ሰላም ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል። መንግሥት የክልሉን ዘላቂ ሰላም የማስጠበቅ ሥራውን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ኀላፊው በመግለጫቸው አንስተዋል፡፡

ትክክለኛውን የፋኖ ስም የማይወክሉ፣ በፋኖ ስም ተደራጅተው በሕዝብ ላይ የተለያዩ ሕገወጥ ድርጊት የሚፈጽሙ ቡድኖችን መንግሥት እንደማይታገስ አቶ ደሳለኝ ገልጸዋል።

ትክክለኛ የፋኖ አባላትን በመንግሥት መዋቅር ሥር በማድረግ እንዲሠሩ እየተደረገ መኾኑንም ኀላፊው አስታውቀዋል።

ዘጋቢ፡-ዳግማዊ ተሰራ

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/