መንግሥት በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል ያጋጠመዉን ችግር በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት እንደሚሠራ የፍትሕ ሚኒስትርና የብልጽግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ጌዲዮን ጢሞቲዮስ (ዶክተር) ገለጹ።

0
232

አዲስ አበባ: ሰኔ 20/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል የተፈጠሩ ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የሚያስችል ዉይይት በብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ እና በማእከላዊ ኮሚቴዉ መካሄዱን የፍትሕ ሚኒስትርና የፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ጌዲዮን ጢሞቲዮስ (ዶክተር) ተናገሩ።
ዶክተር ጌዲዮን ፓርቲው ሰላማዊ ዉይይት ለማድረግ ዉሳኔ አሳልፏል ብለዋል።
በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል የተካሄደው ጦርነት መንግሥት ተገዶ የገባበት መኾኑን ያነሱት የፍትሕ ሚኒስትሩ መንግሥት ይህንን ለመፍታት እየሠራ ስለመኾኑም አስረድተዋል ።
ፓርቲዉ ተጨማሪ ደም መፋሰስ እንዳይኖር ታሳቢ በማድረግ ለሰላም ቅድሚያ ይሰጣል ነው ያሉት።
ዶክተር ጌዲዮን እንዳሉት ፓርቲዉ ባስቀመጠዉ አቅጣጫ መሰረት የሰላም አማራጩ፡-
1. ሕገ መንግሥታዊ እና ሕጋዊነትን የሚያስከብር መኾን አለበት፡፡
2. የሀገርን ክብር የሚያስጠብቅ መኾን አለበት፡፡
3. በሀገር ዉስጥ መፍታት ካልተቻለ በአፍሪካ ሕብረት ጉዳዩ መታየት እንዳለበት በሥራ አስፈጻሚ እና በማእከላዊ ኮሚቴ ዉይይት ዉሳኔ መተላለፉን አንስተዋል።
በተጨማሪም ትንኮሳዎች ካሉ ሕግ አስከባሪዉ እርምጃ እንዲወሰድ ዉሳኔ መተላለፉን ዶክተር ጌዲዮን አንስተዋል። ሕዝቡ ለዚህ ተሳታፊ እንዲኾንም ጥሪ አስተላልዋል።
ዘጋቢ፡- ኤልሳ ጉኡሽ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን‼
ከእኛ ጋር ስለኾኑ እናመሰግናለን‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/