አዲስ አበባ:መጋቢት 07/2015 ዓ.ም (አሚኮ)የሽግግር ፍትሕን የተመለከተ ውይይት እየተካሄደ ነው። ውይይቱ ፍትሕ ሚኒስቴር ከአፍሪካ ኅብረት ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ነው።
የሽግግር ፍትሕን ተግባራዊ ለማድረግ እና ጥሩ የፖሊሲ አማራጭን ለመከተል የሚያግዝ ውይይት እንደኾነ ተገልጿል፡፡
መድረኩ ከዓለማቀፍ ባለሙያዎች ተሞክሮ የሚገኝበት እንደሚሆን በመድረኩ የተገኙት የፍትሕ ሚኒስቴር ሚንስትር ዴዔታ አለምአንተ አግደው ተናግረዋል።
መንግሥት ለሽግግር ፍትሕ መረጋገጥ ቁርጠኛ መሆኑንና ለተቋቋመው ቡድንም ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልጸዋል።
የአፍሪካ ኅብረት ተወካይ ፔሸንስ ቺራይዛ በኢትዮጵያ ሰላምን ለማስፈን ለሚደረገው ጥረት ኅብረቱ ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል።
ይህ ውይይት የተሻለ የፖሊሲ አማራጭ እንዲኖር ግንዛቤ ይገኝበታል ያሉት ተወካዩ የሽግግር ፖሊሲው ለተጎዱ ዜጎች በተለይም ሴቶች ፍትሕ እንዲያገኙ ያግዛል ነው ያሉት፡፡
ዘጋቢ፡- ማርታ ጌታቸው
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!