“መሪህ ከፊት ነው ሕዝብ ሆይ ተነሳ” በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የታሪክ መምህር እና ተመራማሪ ዘመነወርቅ ዮሐንስ (ዶ.ር)

233
ሕዳር 14/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ኢትዮጵያ መልክዓ ምድራዊ አቀማመጧ ያለው ወሳኝነት፣ እጅግ የገዘፈ ታሪክ፣ የቅርስ፣ የባህል እና የዕሴት ባለቤትነቷ፣ የሰው ዘር መገኛ ምድር መሆኗ፣ እምቅ የተፈጥሮ ሃብቷ እና መሰል ገፀ በረከቶቿ ጠላቶቿን አብዝቶታል፡፡ እናም በተለያየ ጊዜ እና ዘዴ የውስጥ ባንዳዎችን የሚጋልቡ የውጭ ጠላቶች የጥፋት እጃቸውን ሲሰነዝሩ ተስተውሏል ሲሉ በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የታሪክ መምህር እና ተመራማሪ ዘመነወርቅ ዮሐንስ (ዶ.ር) አብራርተዋል፡፡
ተመራማሪው እንዳሉት ትላንት አያቶቻችን እንደ አመጣጣቸው አይቀጡ ቅጣት ቀጥተው ያባረሯቸው፣ አንገት ያስደፏቸው፣ ከታሪክ ማማ ያወረዷቸው የእጅ አዙር ቅኝ ገዢዎች ዛሬም ሽብርተኛው የትግራይ ወራሪ ኃይልን በመጠቀም በሀገር ላይ የህልውና አደጋ ደቅነዋል፡፡ ይህ የዘመናችን ከሀዲ ባንዳ እና አሸባሪ የትግራይ ወራሪ ኃይል በሥልጣን ዘመኑ የሠራው ግፍ ይቅር ተብሎ ለሰላም በሃይማኖት አባቶች፣ በሀገር ሽማግሌ እና እናቶች ቢለመን ሀገር የማፍረስ እኩይነቱን አላቆም ብሎ ለገላጋይ ሲያስቸግር ነበር፤ ይባስ ብሎ በዓለም ታሪክ ታይቶ በማይታወቅ ጭካኔ ቤኔቶ ሞሶሎኒን እና ሂትለርን እንኳ ባስናቀ ክህደት የሀገር መከላከያ ሠራዊት ሰሜን ዕዝን ከጀርባ ወጋ፡፡
መንግሥት የሕዝብ ነውና በኀላፊነት እና በሆደ ሰፊነት ከሕግ ማስከበር ዘመቻው በኋላ አሁንም የነገዋን ኢትዮጵያ የአብሮነት ጊዜ ከግምት ውስጥ በማስገባት የተናጠል ተኩስ ውሳኔ አሳልፎ እድል ሰጠ፤ አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ኃይል አፈጣጠሩ ጭምር ለጥፋት እና ሀገር ለማፍረስ ነው እና ሦስተኛ እድሉን ወደ ጎን በመተው በአማራ እና አፋር ክልሎች ወረራ በመፈጸም አሰቃቂ በደሎችን መፈጸም ተያያዘው፤ አሁን ቀይ መስመር ተዘሏል፤ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ከዳር ዳር ተነስቷል።
ዶክተር ዘመነወርቅ ከሌሎች የሥራ ባልደረቦቻቸው ጋር ወደ ጦር ግንባር ለመዝመት መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል፡፡
መምሕሩ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ግንባር እንገናኝ ብለው ያስተላለፉት መልዕክት የአያቶቻቸውን የጀብድ ታሪክ የሚያውቁ እና የሕዝብ ልጅ መሆናቸውን ያሳየ ነው ብለዋል፡፡
መሪ በደግ እና በሰላም ጊዜ ብቻ ሳይሆን ሀገር እንዲህ ዓይነት የህልውና አደጋ ሲደቀንባት ከፊት ሆኖ ሠራዊት መምራት ኢትዮጵያውያን መሪዎች የተለመደ እና ውጤቱም በሀገር ብቻ ሳይሆን በዓለም ደረጃ የሚያስደንቅ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
መሪ ሲቀድም ሕዝብ መከተሉ ታሪካችን ነውና ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያስተላለፉትን መልዕክት ተከትሎ በርካታ ታዋቂ ሰዎች ጭምር ወደ ግንባር መትመም ጀምረዋል፡፡
አሁን የመጨረሻው መጀመሪያ ነው ያሉት ተመራማሪው ውሳኔው የኢትዮጵያን አይበገሬነት፣ አይደፈሬነት፣ አንድነት፣ ቅኝ አለመገዛት፣ ተላላኪ አለመሆን፣ ለሀገር ፍቅር በተግባር የመፋለምን ታሪካዊ ገድላችንን ለቀጣዩ ትውልድ ጭምር እንዲሸጋገር ይረዳል ነው ያሉት፡፡
ሁሉም መሪውን ተከትሎ ታሪካዊ ጠላቱን እስከመጨረሻው ሊያጠፋው ይገባል ብለዋል፡፡
ሽብርተኛው የትግራይ ወራሪ ኃይል በተጨባጭ የተሰጡትን የሰላም አማራጮች ሁሉ መጠቀም የማይችል የጨካኞች ስብስብ በመሆኑ ዳግም የሀገር የቤት ሥራ እንዳይሆን አድርጎ ማጥፋት ግድ እንደሚል ነው የተናገሩት፡፡
“መሪህ ከፊት ነው ሕዝብ ሆይ ተነሳ” ብለዋል ዶክተሩ፡፡
ዶክተር ዘመነወርቅ ወቅቱን ኢትዮጵያዊ ሁሉ የአያቶቹን ታሪክ የሚደግምበት እና ወርቃማ ታሪኩን የሚጽፍበት አጋጣሚ ሲሉ ገልጸውታል፡፡ ኢትዮጵያ እየተፋለመች ያለችው በእጅ አዙር ቅኝ ለመግዛት በቀጥታ እየተሳተፉ ካሉ አንዳንድ ምዕራባውያን ሀገራት ጋር ጭምር ስለሆነ በክተት ጥሪው አፍሪካውያን ጭምር ሊሳተፉ ይገባል፡፡ ኢትዮጵያ የአፍሪካ የነጻነት ቀንዲል በመሆኗ ሁሉም አፍሪካዊ ከኢትዮጵያውያን ጎን በመቆም የዚህ ድል ተካፋይ እንዲሆኑ ዕድሉን ሊጠቀሙበት ይገባል የዶክተሩ ማብራሪያ ነው፡፡
ዘጋቢ፡-የማነብርሃን ጌታቸው
ተነሳ!!
መሪህን ተከተል!!
ሀገርህን አድን!!
ነፃነትህን አትስጥ !!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ