“መላ ኢትዮጵያውያን ከውስጥም ከውጭም ያሉብንን ጠላቶች ለመመከት በአንድነት ልንቆም ይገባናል” ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ

96

ታኅሣሥ 03/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የአዲስ አበባ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አባላት በወሎ ግንባር በመገኘት የወገን ጦርን አበረታተዋል፤ ለወገን ጦርም ከ18 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አድርገዋል፡፡

በወሎ ግንባር የተገኙት የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ዶክተር አረጋዊ በርሄ እንደተናገሩት እኛ ኢትዮጵያውያን ስንተባበር ለጠላቶቻችን አስፈሪ እንሆናለን፤ኢትዮጵያውያን በአንድነት ስንቆም አይደለም ለሀገር ውስጥ ጠላት ይቅርና ለውጭ ጠላት የማንሸነፍ ሕዝቦች ነን ብለዋል፡፡

ጠላቶች ኢትዮጵያን ለመድፈር ያልተሳካላቸው በአንድነት ስለመከትናቸው ነው ያሉት ዶክተር አረጋዊ ጣሊያን ኢትዮጵያን ለመውረር ሲመጣ ቀደምት አባቶች ያሳፈሩት በአንድነት በመቆማቸው እንደሆነ ልብ ሊባል እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ በበኩላቸው ወቅቱ ኢትዮጵያን በማዳንና ኢትዮጵያን ለማፍረስ በሚታትሩ ኃይሎች መካከል ጦርነት እየተደረገበት ያለ መሆኑን አንስተዋል፡፡ “መላ ኢትዮጵያውያን ከውጭም ከውስጥም ያሉብንን ጠላቶች ለመመከት በአንድነት ልንቆም ይገባናል” ብለዋል፡፡

በወሎ ግባር ከጠላት ጋር እየተፋለመ ለሚገኘው የወገን ጦር በግንባር ተገኝተው ያበረታቱት ፖለቲከኞቹ ለሠራዊቱ ድጋፍ ማድረግም ይገባል ነው ያሉት፡፡

በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በዲፕሎማሲው ዘርፍ እየተጫወቱት ያለው ሚና እጅግ የሚያኮራ እንደሆነም ተነስቷል፡፡ ይህንን ርብርብ በማጠናከር ኢትዮጵያ አሸናፊ እንድትሆን መሥራት ያስፈልጋልም ተብሏል፡፡

አንጋፋ ፖለቲከኞቹ የሀገር ኩራት የሆነው የወገን ጦር እያደረገ ላለው ተጋሎ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

ዘጋቢ፡- ኤልያስ ፈጠነ – ከወሎ ግንባር

#ተነሳ!!
#መሪህን ተከተል!!
#ሀገርህን አድን!!
#ነፃነትህን አትስጥ !!
#አካባቢህን ጠብቅ!!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation