“ሕዝቡ እንደቀድሞው ለመኖር የሚያስችለው የማኅበራዊ ገመድ አሁንም አለ” የማኅበራዊ ሳይንስ ምሁር

55
ነጭመደበኛ
ነጭመደበኛ

ባሕር ዳር፡ መጋቢት 28/2014 ዓ.ም (አሚኮ) አሸባሪው ትህነግ በአገዛዝ ዘመኑ ኢትዮጵያዊያንን በሐሰት ትርክት የመለያየት ሴራን በመቅረፅ የራሱን የፖለቲካ ዓላማ ለማስፈጸም ከፍተኛ ሥራ ሠርቷል፡፡ ከአንድነት ይልቅ ልዩነትን በመስበክ ለዘመናት በአንድነትና በፍቅር ሲኖር የነበረ ሕዝብን እንዲለያይ የመከፋፈል አጀንዳ ቀርጾም ሢሠራ ቆይቷል፡፡ በኢትዮጵያዊያን የነጻነት ትግል የማፍያ ቡድኑ ከሥልጣን ከተወገደ ኋላም አጀንዳውን የሚፈጽሙለት ተላላኪ ቡድኖችን በማደራጀትና በመደገፍም በንጹሃን ኢትዮጵያዊያን ላይ ከፍተኛ ግድያ፣ የሀብት ውድመት፣ ሥደትና መፈናቀል እንዲፈጸም አድርጓል፡፡ አሸባሪ ቡድኑ አሁንም የመከፋፈል ሴራውን በመጠቀም ኢትዮጵያን በማፍረስ ሕዝቧን ሀገር አልባ ለማድረግ እየታተረ ይገኛል፡፡
አሚኮ ያነጋገራቸው በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የማኅበራዊ ሳይንስ መምህር በቀለ መለሰ (ዶክተር) አሁን ላይ በኢትዮጵያ እየተፈጸመ ላለው የንጹሃን ሞት፣ መፈናቀልና የሀብት ውድመት መንስኤው አሸባሪው ትህነግ እንደሆነ ያስረዳሉ፡፡ ቡድኑ በሴራ ፖለቲካ የተከፋፈለ ማኅበረሰብ እንዲፈጠር ለረዥም ጊዜ በመሥራቱ አሁንም ችግሩ ቀጥሏል የሚሉት ምሁሩ ሕዝቡ እንዳይተማመን፤ አንዱ ሌላውን በጥርጣሬ እንዲመለከተው አድርጓል ብለዋል፡፡
አሸባሪው ቡድን የማኅበረሰቡን አንገብጋቢ ችግሮች በመፍታት ሀገር መገንባት ሲያቅተው እኩይ ዓላማውን ለማሳካት ማኅበረሰቡን በዘር በመከፋፈል ስልጣኑን ለማራዘም በመጣሩ ችግሩ መባባሱን አስገንዝበዋል፡፡ ከችግሩ ለመውጣት ሁሉም ማኅበረሰብ ቆም ብሎ ማኅበራዊ እሴቱን ማስተዋል እና አንዱ ለሌላው ማሰብ እንደሚጠይቀው ምሁሩ አስገንዝበዋል፡፡ በሀገር መንግሥት ግንባታ አማራ በተለያዩ አካባቢዎች እንዲኖር ኾኗል የሚሉት ዶክተር በቀለ ሌላው ማኅበረሰብ አሸባሪው ቡድን በነዛው የሐሰት ትርክት ምክንያት በአማራ ላይ ጥቃት እንዲደርስ መሥራቱን ገልጸዋል፡፡ አሁን ላይ በተለያየ አቅጣጫ በተሠራበት የሐሰት ትርክት ጥቃት እየደረሰበት እንደሆነም ተናግረዋል፡፡
የችግሩ መሰረታዊ ጉዳይ የሚፈታው የተሠራው የሐሰት ትርክት ሲስተካከል እና እየተሄደበት ያለው መንገድ የተሳሳተ መሆኑን የፖለቲካ ልሂቃን በኀላፊነት መሥራት ሲችሉ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የሕዝብ የቀደመ ተባብሮ የመኖር እና የመደጋገፍ ማኅበራዊ እሴት እንዲመለስ ፖለቲከኞቹ ጠንክረው ሊሠሩ እንደሚገባም አስገንዝበዋል፡፡
በተለይም የዘር ፖለቲካን የሚሰብከው ሕገመንግሥት እንዲሻሻል በመማድረግ መፍትሄ ማምጣት እንደሚያስፈልግም ምሁሩ ተናግረዋል፡፡
ፖለቲከኞች ላይ አለመስማማት ሲፈጠር የሕዝብ ማኅበራዊ እሴት ሲናጋ እና ችግር ሲፈጠር መመልክት የተለመደ ክሰተት ኾኗል የሚሉት ምሁሩ ፖለቲከኞች የሚፈልጓቸውን ሐሳቦች በሕዝብ ጀርባ ተጠልለው ከማስፈጸም መውጣት ካልቻሉ ችግሮችን በቀላሉ መፍታት አስቸጋሪ እንደሚያደርገው አብራርተዋል፡፡ ፖለቲከኞችም በመቻቻል መርህ ሕዝብን መምራት እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል፡፡
መንግሥት ችግሩን ከሥረ መሠረቱ መፍታት ይጠበቅበታል የሚሉት ምሁሩ እንደመፍትሔ ብሔራዊ የምክክር መድረኩ ላይ ብስለት በተሞላበት መንገድ የሐሰት ትርክቶች እንዲጠፉ በመምክር ወደ መፍትሔ ሐሳብ መምጣት እና የማኅበረሰቡን አብሮ የመኖር እሴት ማዳበር እንደሚያስፈልግ ነው የገለጹት፡፡ ፖለቲከኞች ብስለት በተሞላበት መንግድ ሕዝብን መምራት ከቻሉ ሕዝቡ እንደቀድሞው ለመኖር የሚያስችለው የማኅበራዊ ገመድ አሁንም አለ ብለዋል፡፡
ዘጋቢ፡-ምሥጋናው ብርሃኔ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/