“ልዩ ኀይላችን በተግባር መስዋዕትነት እየከፈለ ኢትዮጵያን ከመፍረስ እና ከመበታተን የታደገ ኃይል ነው” የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ወርቁ ኀይለማርያም

0
179

“ልዩ ኀይላችን በተግባር መስዋዕትነት እየከፈለ ኢትዮጵያን ከመፍረስ እና ከመበታተን የታደገ ኃይል ነው” የማዕከላዊ ጎንደር ዞን
ዋና አስተዳዳሪ አቶ ወርቁ ኀይለማርያም
ባሕር ዳር: መጋቢት 16/2013 ዓ.ም (አብመድ) የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ወርቁ ኀይለማርያም በ5ኛው
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 11ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ የአማራ ልዩ ኃይልን በተመለከተ ሁለት የምክር
ቤት አባላት ያነሱትን ሀሳብ ኢትዮጵያውያንን ለመበታተን እና ለማፈራረስ የሚታትሩ ኃይሎች የተቀነባበረ አጀንዳ መሆኑን
አስገንዝበዋል።
የአማራ ልዩ ኃይል እውነተኛ ሕብረ ብሔራዊ ፌዴራሊዝም ለመገንባት መሰዋዕትነት እየከፈለ ያለ እውነተኛ የኢትዮጵያ የቁርጥ
ቀን ሰራዊት እንደሆነ ነው የተናገሩት።
ዋና አስተዳዳሪው የልዩ ኃይሉ ጀግንነትም ሆነ ጥንካሬ ሚስጥሩ የአማራ ሕዝብ ለሀገረ መንግሥታት ምሥረታ በደሙ የከፈለው
መሰዋዕት ውርስ ነው ብለዋል ።
ዋና አስተዳዳሪው እንዳሉት የአማራ ልዩ ኃይልና ሚሊሻ ለአማራ ሕዝብ ብቻ ሳይሆን ለኢትዮጵያ ህዝብም ዋልታና ማገር መሆኑን
በተግባር ያረጋገጠ ኃይል ነው፤ የአማራ ልዩ ኃይልና ሚሊሻ በሕግ ማስከበር ዘመቻም ሆነ በሀገሪቱ በተለያዩ ጊዜያት
በሚያጋጥሙ የፀጥታ ችግሮች የመፍትሔ አካል ሆነው ከፊት በመሰለፍ አኩሪ ጀብድ እየፈጸሙ ያሉና ለህይዎት ሳይሳሱ
መሰዋዕት በመክፈል ኢትዮጵያን ከመፈራረስ እና ከመበታተን የታደጉ ናቸው።
የአማራ ልዩ ኋይል ሕዝብንና ሀገርን በፍትሐዊነት፣ በእኩልነትና በሀቀኝነት በማገልገል ለእዉነትተኛ ፌዴራሊዝም ሌት ከቀን
እየሠራ ያለ ሰራዊት መሆኑንም አስገንዝበዋል።
ልዩ ኃይሉ በከፈለዉ የህይዎት መስዋዕትነትም በሀገር ሉዓላዊነት ላይ የተጋረጠውን ጥቃት መክቶ ሀገርንና ሕዝብን ከመበተን
ታድጓል፤ ይህ ታሪክ የማይረሳው ነው ብለዋል።
አንዳንድ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በፓርላማ ውስጥ ያራገቡት ሀሳብ የተላላኪነት ሚናችውን ለመጫወት ካላቸው
ፍላጉት የመነጨ በመሆኑ የሰም ማጥፍት ዘመቻውን እንደሚቃወሙ ነው ያሳሰቡት።
ስለ ልዩ ኃይሉ ግብረ-ገብነትና ሕዝባዊነት በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል በተወሰደዉ ሕግ ማስከበር ዘመቻ ወቅት የሀገር መከላከያ
ሠራዊትና የጁንታው ምርኮኞች በተግባር ያረጋገጡት እውነታ መሆኑን ጠላትም ወዳጅም አረጋግጧል ብለዋል።
ልዩ ኃይሉ ላይ የተነሳው የስም ማጥፋት ዘመቻ ሀገርና ሕዝብ ለመበተን ቆርጠው የተነሱ ጽንፈኛ ተላላኪ ኃይሎች ሴራ እንጂ
የአማራ ልዩ ኃይል ስሙ የአማራ ይሁን እንጂ ግብሩና ተግባሩ ኢትየጵያዊ መሆኑን ተናግረዋል።
የአማራ ልዩ ኃይል የጁንታው እብሪት ጫፍ ደርሶ ሀገርና ሕዝብን ለማፍረስ ሲነሳ በተጠና መልኩ በሀገር መከላከያ ሠራዊት ላይ
ክህደት ሲፈጽም ደርሶ መስዋዕትነት ከፍሎ ደጀን የሆነ ኃይል ነው፡፡ በከፈለው መሰዋዕትነትም የክልሉ ሕዝብ ብቻ ሳይሆን
የኢትዮጵያ ሕዝብ አሁን ለደረሰበት ደረጃ እንዲደርስ ታሪክ የማይረሳው አኩሪ ጀግንነት ፈጽሟል ነው ያሉት ፡፡
ልዩ ኃይሉም በጽንፈኞች አሉባልታ ሳይገታ ለእውነተኛ ፌዴራሊዝም፣ ለፍትሕ እና ለእኩልነት የሚያደርገውን ትግል አጠናክሮ
እንደሚቀጥል አስገንዝበዋል። ምንጭ: የማዕከላዊ ጎንደር ዞን የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ማህበራዊ ትስስር ገጽ ነው
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here