“ሊካሄድ የታሰው ሀገር አቀፍ ምክክር የሕዝብን ጥያቄ መሰረት ያደረገ ከኾነ የታሰበው ውጤት ይመጣል” የፖለቲካ ሳይንስ መምህር

0
165

የካቲት 09/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ሀገር አቀፍ ምክክሩ በተሳካ መንገድ ይካሄድ ዘንድ ምክክሩን የሚመራ ኮሚሽን በመቋቋም ሂደት ላይ ነዉ፡፡ ይህንን ጉዳይ በተመለከተ ከአሚኮ ጋር ቆይታ ያደረጉት በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ መምህሩ ሐሳቡ ተስፋ የምክክር መድረኩ የመጨረሻ ግብ ሀገራዊ አንድነትን ማምጣት ነዉ ብለዋል፡፡

“ሀገራዊ አንድነትን ማምጣት ዓላማ ያደረገ የምክክር ኮሚሽን ከሂደቱ ጀምሮ የተጠና ሥራ መሥራት ይጠበቅበታል” ነው ያሉት፡፡

ሀገር አቀፍ ምክክሮች በተለያዩ ሀገራት የመካሄድ ልምድ መኖሩን ያነሱት መምህሩ በአንዳንድ ሀገራት የታሰበውን ውጤት ሲያሳካ በጥቂት ሀገራት ደግሞ ስኬታማ አለመኾኑን ተናግረዋል። በሀገራዊ ምክክር ወቅት ውጤት ያገኙ ሀገራት ከምክክሩ በፊት መሥራት የሚገባቸውን ተግባራት አስቀድመው በማከናወን ሀገር አቀፍ ጉዳዮችን በአፅንዖት ለይተው በመወያየታቸው እንደኾነ ገልጸዋል።

በመደማመጥ መፍትሔ ላይ መሥራት ከተቻለ በውይይት ለውጥ ካመጡት ሀገራት ተሞክሮ መውሰድ እንደሚቻል ነው ያስረዱት።

በተቃራኒው ከቅድመ ውይይት ጀምሮ እስከ ተግባር ምዕራፍ ድረስ የሀገራዊ ምክክር መድረክን ፅንሰ ሐሳቦች ያልተከተሉ ሀገራት ያሰቡትን ሳያሳኩ መቅረታቸውን አንስተዋል።

በኢትዮጵያ ሊካሄድ የታሰበዉ ሀገር አቀፍ የምክክር መድረክ ስኬታማ ይኾን ዘንድም የዜጎች መሰረታዊ ጥያቄዎች አካታችነት ላይ በትኩረት ሊሠራ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

“በምክክሩ የመላ ሀገሪቱ ትላልቅ ችግሮች እንደሚመከርባቸው በመገንዘብ የሐሳብ አካታችነቱ ላይ ሊታሰበብበት ይገባል” ነዉ ያሉት፡፡

ምክከሩ በሊሂቃን ሳይኾን በሕዝብ ፍላጎት ላይ ተመስርቶ እንዲደረግ የኮሚሽኑ አባላት ኾነዉ የተመረጡ አካላት ለተደራሽነቱና ለመሰረታዊ ጥያቄዎች ምላሽ አፅንኦት መስጠት ይጠበቅባቸዋል ነዉ ያሉት፡፡

ኮሚሽኑ ሕዝባዊ ቅቡልነት እንዲኖረዉ የሕዝብን ጥቅም መሰረት ያደረገ፣ በገለልተኝነት፣ በታማኝነት፣ በግልጸኝነት ሥራውን መፈጸም ይኖርበታል ብለዋል፡፡

ዘጋቢ፡- ኤልያስ ፈጠነ

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/