“ለጋራ ሀገር በጋራ መቆም ይገባል” አስተያየት ሰጭዎች

0
24

“ለጋራ ሀገር በጋራ መቆም ይገባል” አስተያየት ሰጭዎች
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 14/ 2013 ዓ.ም (አሚኮ) ተፎካካሪ ፓርቲዎች በመቻቻል እና በመደማመጥ ላይ የተመሠረተ ግንኙነትን
በማጠናከር ለአንድ የጋራ ሀገር ዘብ ሊቆሙ እንደሚገባ በምዕራብ ጎንደር ቋራ ወረዳ የገለጉ ነዋሪዎች ጥሪ አቅርበዋል።
የፖለቲካ ፓርቲዎች ሰላም የሰፈነባት እና ፍትሐዊ ልማት የተረጋገጠባት ጠንካራ ሀገር ለመገንባት መሥራት እንደሚገባቸው ነው
ነዋሪዎች የተናገሩት።
ድምጻቸውን በሰጡበት የምርጫ ጣብያ ምርጫው በሰላም መጠናቀቁን የገለጹት አስተያየት ሰጭዎች በድሕረ ምርጫም ሁሉም
የፖለቲካ ፓርቲዎች ለሰላም ዘብ ሊቆሙ እንደሚገባ መክረዋል።
አስተያየት ሰጭዎች እንዳሉት አሸናፊው ፓርቲ ሁሉም ዜጎች በነጻነት ተዘዋውረው መሥራት የሚችሉባት ሀገር ግንባታ ላይ
ትኩረት ሰጥቶ መሥራት ይጠበቅበታል፤ ተሸናፊ ፓርቲዎች ደግሞ በቀጣይ ምርጫ ለማሸነፍ መዘጋጀት እና በሀገር አንድነት ላይ
በትብብር መሥራት እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል።
ልዩነቶችን በመቻቻል እና በመነጋገር ለአንድ የጋራ ሀገር ግንባታ መቆም እንደሚገባም መክረዋል። ማኀበረሰቡም ተደራጅቶ
አካባቢውን በመጠበቅ ልማቱ ላይ ማተኮር እንዳለበትም ለአሚኮ ተናግረዋል። አሁን ሀገሪቱ ያለችበትን ነባራዊ ሁኔታ መረዳት
እንደሚገባም መክረዋል። እነሱም አካባቢያቸውን ነቅተው በመጠበቅ የዜግነት ግዴታቸውን እንደሚወጡ ነው የገለጹት፡፡
ዘጋቢ፦ ዳግማዊ ተሠራ – ከቋራ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here