ለወራት ዝግ የነበረው የመተማ -ገላባት መንገድ ክፍት ኾኖ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ተጀመረ።

0
370

የካቲት 23/2014 ዓ.ም (አሚኮ) አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ኃይል በከፈተው ጦርነት ምክንያት ለ7 ወራት ተቋርጦ የነበረው የመተማ -ገላባት መንገድ ክፍት ኾኖ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ተጀምሯል።

የገላባት ጉምሩክ ኃላፊ ኮሌኔል ሙሐመድ አብዲል ማዲድ በቀጣናው የሚታዩ የጸጥታ ችግሮችን ለመፍታት በጋራ መሥራት እንደሚገባ ተናግረዋል።

ለጋራ ደኅንነት የመረጃ ልውውጥና የጋራ ቅኝት ማድረግ እንደሚገባም ገልጸዋል።

የመንግሥት ኃላፊነት የሕዝቦችን ደኅንነት መጠበቅ ነው ያሉት የመተማ ዮሐንስ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ደኅንነት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ጌጡ ዔለሜ በበኩላቸው በቀጣናው የሚስተዋሉ ወንጀሎችን ለማስቆምና አካባቢውን ፍጹም ሰላማዊ ለማድረግ በጋራ እንሠራለን፤ የንግድ ትስስራችንም አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል።

የሁለቱንም ወንድም ሕዝቦችን መልካም ግንኙነት የሚያሻክሩ ጸረ ሰላም ኃይሎችን በጋራ መዋጋት አለብን ነው ያሉት። በሱዳን መጠለያ ካምፕ ውስጥ በጥገኝነት ሥም የተጠለሉ የጽንፈኛው የቅማንት ታጣቂ ቡድንና እና የአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን አባላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ኃላፊነቱ መውሰድ አለባችሁ ብለዋል።

የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው በሀገራቱ መካከል የቆየውን መልካም ግንኙነት አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባና ገልጸዋል።

የሚያጋጥሙንን ችግሮች በጋራ ውይይት መፍታት አለብን ያሉት ተሳታፊዎቹ ጽንፈኛውን የቅማንት ታጣቂ ቡድንና አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን በጋራ ለመዋጋት ጥቆማ ክትትልና ቁጥጥርም እንደሚያደርጉ ነው የገለጹት።

ከዛሬ ጀምሮ የንግድ እቃዎችን ማስገባትና ማስወጣት እንደሚችል የተገለጸ ሲኾን ኅብረተሰቡ ከጠዋቱ 1:00 ስዓት እስከ 11:30 እንዲንቀሳቀስም የስዓት ገደብ ተጥሏል።

ዘጋቢ:- ቴዎድሮስ ደሴ – ከመተማ ዮሐንስ

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/