ለኢንዱስትሪ ሽግግር ዩኒቨርሲቲዎች የንድፈ ሃሳብ ትምህርትን ከተግባር ጋር በማዋህድ መስጠት እንዳለባቸው የኢትዮጵያ ቴክስታይል እና ፋሽን ቴክኖሎጅ ኢንስቲትዩት ገለጸ፡፡

0
38

ለኢንዱስትሪ ሽግግር ዩኒቨርሲቲዎች የንድፈ ሃሳብ ትምህርትን ከተግባር ጋር በማዋህድ መስጠት እንዳለባቸው የኢትዮጵያ
ቴክስታይል እና ፋሽን ቴክኖሎጅ ኢንስቲትዩት ገለጸ፡፡
ባሕር ዳር፡ ግንቦት 13/2013 ዓ.ም (አሚኮ) ዘጠነኛው የጨርቃጨርቅ እና ፋሽን ቴክኖሎጅ ዓለም አቀፍ ኮንፈረንስ በባሕር ዳር
እየተካሄደ ነው። በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ቴክስታይል እና ፋሽን ቴክኖሎጅ ኢንስቲትዩት ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር አበራ
ከጪ (ዶክተር ) እንዳሉት የኢትዮጵያ ቴክስታይል እና ፋሽን ቴክኖሎጅ ዘጠነኛ ጉባኤ ትኩረት ያደረገው የጨርቃጨርቅ እና
አልባሳት ኢንዱስትሪውን ለማሳደግ ከኢንዱስትሪ ባለሙያዎች፣ ከፖሊሲ አውጭዎች፣ መንግሥታዊ እና መንግሥታዊ ካልሆኑ
ድርጅቶች ጋር በመተባበር በጋራ ለመሥራት ነው፡፡
ዶክተር አበራ የጨርቃጨርቅ እና አልባሳት ዘርፍ ከግብርና ወደ ኢንዱስትሪ ለመሸጋገር እንደ ድልድይ እንደሚያገለግል ገልጸዋል፡፡
እንደ እንግሊዝ፣ አሜሪካ፣ ጃፓን፣ ቻይና የመሳሰሉ የአደጉ ሀገሮች የእድገታቸው መነሻ ለዘርፉ ትኩረት መስጠታቸው እንደኾነም
አስረድተዋል፡፡ ኢትዮጵያም ለኢንዱስትሪ ሽግግር ትኩረት ሰጥታ እየሠራች መሆኑን ጠቅሰዋል። ለዚህ ደግሞ የባሕርዳር
ዩኒቨርሲቲ የማነሳሳት ሥራ እየሠራ ይገኛል ብለዋል።
ከዩኒቨርሲቲዎች ተመርቀው የሚወጡ ተማሪዎች ሥራ ፈላጊ ሳይሆኑ ሥራ ፈጣሪ እንዲሆኑ የንድፈ ሃሳብ ትምህርት ከተግባር ጋር
በማዋህድ መስጠት እንደሚገባም ተመላክቷል፡፡ ዘርፉን ለማሳደግ ሀብትን ከእውቀት ጋር ማቀናጀት እንደሚገባም ዳይሬክተሩ
ተናግረዋል፡፡ የጨርቃጨርቅ እና አልባሳት ኢንዱስትሪውን ለማሳደግ በሚደረገው ጥረት ከዩኒቨርሲቲው ጋር የሚሠሩ አካላት
ቁጥር እየጨመረ እንደሚገኝም ገልጸዋል፡፡
የኢትዮጵያ ጨርቃጨርቅ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ስለሽ ለማ የጭርቃጨርቅ እና አልባሳት ዘርፉ ከፍተኛ
የሥራ ዕድል ለመፍጠር ካለው ምቹ ሁኔታ አኳያ ዓለምአቀፍ ጉባኤ መካሄዱን ገልጸዋል፡፡
በጉባኤው ዓለም አቀፍ ተሞክሮዎች እና ጥናቶች በመቅረባቸው ተሞክሮዎች ከሀገሪቱ ተጨባጭ ሁኔታ ጋር እየታዩ ተግባራዊ
እንደሚደረጉ አቶ ስለሽ ጠቅሰዋል፡፡ ዘርፉ ተማሪዎች በንድፈ ሀሳብ ያገኙትን እውቅት ወደ ተግባር እንዲለውጡ እድል ይሰጣል
ብለዋል፡፡
ዋና ዳይሬክተሩ ሀገሪቱ በዘርፉ ላይ የደረሰችበትን የእድገት ደረጃ እና እየተከተለች ያለውን ስትራቴጅ ለማካፈልና ከሌሎች
ሀገራት ደግሞ ተሞክሮ የሚቀሰምበት መድረክ እንደሆነ አንስተዋል፡፡ ባለሃብቶችን ለመሳብ ጉባኤው እንደሚጠቅምም
ጠቅሰዋል፡፡
በቀጣይ ከዩኒቨርሲቲዎች ጋር በመማር ማስተማር፣ በምርምር እና በማኅበረሰብ አቀፍ አገልግሎት ላይ በትብብር ለመስሥራት
የሚያስችል ስምምነት እንደተደረገም ገልጸዋል፡፡ ዘርፉ በመንግሥትም ትኩረት ተሰጥቶት እንየተሠራ እንደሚገኝ ዳይሬክተሩ
ተናግረዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ዳግማዊ ተሠራ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here