“ለአማራ ሕዝብ ስንል የምንከፍለው ማንኛውም ዓይነት መስዋዕትነት ለኛ ቢያንስ እንጂ አይበዛም” የአማራ ልዩ ኀይል 29ኛ ጣና ብርጌድ ሁለተኛ ሻለቃ አባላት

0
165

“ለአማራ ሕዝብ ስንል የምንከፍለው ማንኛውም ዓይነት መስዋዕትነት ለኛ ቢያንስ እንጂ አይበዛም” የአማራ ልዩ ኀይል 29ኛ ጣና
ብርጌድ ሁለተኛ ሻለቃ አባላት
ባሕር ዳር: ሐምሌ 11/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ልዩ ኀይል ለአማራ ሕዝብ መሞት ክብሩ መሆኑን የ29ኛ ጣና ብርጌድ
ሁለተኛ ሻለቃ የልዩ ኀይል አባላት ገልጸዋል፡፡
አሸባሪው ትህነግ ከአማራ ሕዝብ ጋር የሚያወራርደው ሒሳብ እንዳለው ቢገልጽም የሚያወራርደው ሳይኾን የሚዋረድበት ሒሳብ
እንዳለው ነው የልዩ ኀይል አባላቱ የተናገሩት፡፡
ዋና ሳጅን በሪሁን ወንዴ የአማራ ልዩ ኀይል ጣና 29ኛ ብርጌድ ሁለተኛ ሻለቃ አባል ናቸው፡፡ ዋና ሳጅን በሪሁን እንዳሉት የአማራ
ልዩ ኀይል ከእውነተኛ ኢትዮጵያዊነትና ከአማራ አብራክ ወጥቶ ታላላቅ ገድሎችን እየፈጸመ የሚገኝ ኃይል ነው፡፡ ለአማራ ልዩ
ኀይል የትኛውንም ዓይነት ወታደራዊ ግዴታዎች ይሰጠው በአስደናቂ ብቃት ይፈጽማል ነው ያሉት፡፡
ትህነግ ከውልደቱ እስከ ዕድገቱ በእብሪት የተሞላ እንደኾነም ነው የገለጹት፡፡ትህነግ የሚያወራውን የሚሠራ ሳይኾን በምኞት
ብቻ የሚኖር መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
ትህነግ ከአማራ ሕዝብ ጋር የማወራርደው ሒሳብ አለኝ ቢልም እኛ ጋር ያላቸው የሚያወራርዱት ሒሳብ ሳይኾን የሚዋረዱበት
ሒሳብ ብቻ ነው ብለዋል፡፡
ለአማራ ሕዝብ ሲባል የሚከፈለው ማንኛውም ዓይነት መስዋዕትነት ለልዩ ኀይሉ ቢያንስ እንጂ አይበዛም ነው ያሉት፡፡
የአማራ ሕዝብ ለሠራዊቱ እያደረገ ያለው ሁለንተናዊ ድጋፍ እንደ ልዩ ኀይል በራሱ መታደል፣ መሰጠት ወይም መሸለም
እንደኾነም ነው ዋና ሳጅን በሪሁን የገለጹት፡፡
ኮንስታብል ጠጄ አዲስ የአማራ ልዩ ኃይል 29ኛ ብርጌድ ሁለተኛ ሻለቃ አባል ናት፡፡ “ለአማራ ሕዝብ ከተባልኩኝ የምቆጥበው
አንዳችም ነገር የለኝም” ነው ያለችው፡፡
ሌላው አባል ዋና ሳጅን ጥላሁን ንብረት በበኩላቸው “የአማራ ልዩ ኀይል እና ጀግንነት የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች ናቸው”
ይላሉ፡፡
የአማራ ልዩ ኀይል የአማራን ሕዝብ ህልውና ለማስጠበቅ ብቻ ሳይሆን የሀገር ህልውናን ለማስጠበቅ ሲል የማይከፍለው
መሰዋዕትነት እንደሌለም አብራርተዋል፡፡ ለዚህም አሸባሪው ትህነግ በመከላከያ ሠራዊት ላይ ላደረሰው ጥቃት የሰጠውን ምላሽ
ማየት በቂ ነው ብለዋል፡፡
የአማራ ጠላት የሆነውን አሸባሪው ትህነግ እስከ ወዲያኛው ለመሸኘት የአማራ ልዩ ኀይል ከበቂ በላይ ተዘጋጅቷል ነው ያሉት፡፡
የአማራን ሕዝብ ደጀን አድርጎ በየትኛውም አውደ ውጊያ ላይ መሸነፍ የማይታሰብ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
የአማራ ልዩ ኀይል ሀገርንና አማራነትን ማስከበር የሚል ትልቅ ዓላማን ያነገበ ነው፤ ለአማራ ሕዝብ ሲባል መሞት ኩራት ነው
ብለዋል።
ሻለቃ አማረ መልካሙ የ29ኛ ጣና ብርጌድ ሻለቃ አዛዥ ናቸው፡፡ የአማራ ልዩ ኀይልን መምራት በራሱ ትልቅ ዕድል መሆኑን
ገልጸዋል፡፡ ሻለቃ አማረ እንደተናገሩት የአማራ ልዩ ኀይል የአማራን ሕዝብ ሉዓላዊነት ማስከበር ብቻ ሳይኾን የሀገር
ሉዓላዊነትንም ለማስከበር ግዳጅ ወስዶ የሚንቀሳቀስ ከበቂ በላይ ቁመና ያለው ኀይል ነው፡፡ አሸባሪው የትህነግ ቡድን የአማራን
ልዩ ኀይል ጠንቅቆ ስለሚያውቀው በእጅጉ ይፈራዋል ያሉት አዛዡ እብሪተኛውን ትህነግም ለመቅጣት ዝግጁዎች እንደሆኑ
ተናግረዋል፡፡
ዘጋቢ:- እሱባለው ይርጋ – ከዋግ ኽምራ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here