ትናንት በስፔን ቫሌንሻ በተደረገ የ5 ሺህ ሜትር የሩጫ ውድድር ለተሰንበት ግደይ ለ12 ዓመታት በጥሩነሽ ዲባባ ተይዞ የነበረውን ክብረወሰን በማሻሻል አሸንፋለች።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶክተር) አትሌት ለተሰንበት ግደይ አዲስ ክብረ ወሰን በማስመዝገቧ ተሰማቸውን ደስታ በትዊተር ገጻቸው ገልጸዋል፡፡
በዚሁ በቫሌንሽያ በተደረገ የወንዶች ውድድር ዩጋንዳዊው አትሌት ጆሽዋ ቼፕቴጌ በአትሌት ቀነኒሳ በቀለ ለ15 ዓመታት ተይዞ የነበረውን የ10 ሺህ ሜትር ክብረ ወሰን ሰብሯል፡፡ አትሌቱ የገባበት ሰዓትም 26፡11፡02 ሆኖ ተመዝግቧል፡፡