“ለሰላም ስምምነቱ ተፈጻሚነት መንግስት ቁርጠኛ ነው” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን

0
64

አዲስ አበባ: ሕዳር 08/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የአውሮፓ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ከዶክተር አኔት ዌበር ጋር በጽሕፈትቤታቸው በሰላም ስምምነት እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል፡፡

በወቅቱም አቶ ደመቀ የኢትዮጵያ መንግሥት የሰሜኑን ችግር በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ካለው ፍላጎት መነሻነት የሰላም ስምምነት እንዲደረስ በትኩረት ሲሠራ እንደነበር አንስተዋል።
ለተግባራዊነቱም ቁርጠኛ መሆኑን ገልጸዋል።

ግጭት ተፈጥሮባቸው በነበሩ አካባቢዎች ላሉ ወገኖች የሰብዓዊ ዕርዳታ ተደራሽ እየተደረገ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ መሠረታዊ አገልግሎቶች የማስጀመሩ ሥራ ተጠናክሮ መቀጠሉንም አብራርተዋል፡፡

በተያያዘም በሀገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች የሚታዩ የፀጥታ ችግሮችን ለመፍታት መንግሥት ከሚመከታቸው አካላት ጋር ፖለቲካዊ ውይይት እንደሚያደርግ እንዲሁም በብሔራዊ ምክክር መድረክ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ውይይቶች እንደሚካሄዱ ገልጸዋል፡፡

የሰላም ስምምነት እንዲፈረም ድጋፍ ላደረጉ አካላት ምሥጋና አቅርበው በቀጣይም በስምምነቱ ትግበራ ምዕራፍ እና መልሶ ማቋቋሙ ላይ አጋር አካላት ትብብራቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ አቶ ደመቀ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የአውሮፓ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ከዶክተር አኔት ዌበር በበኩላቸው የተደረሰው የሰላም ስምምነት ታሪካዊ ነው ብለዋል፡፡ የአውሮፓ ሕብረትም ለስምምነቱ ተግባራዊነት እና መልሶ ማቋቋም በተመለከተ የድርሻውን ሚና እንደሚወጣ መግለጻቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ ያመላክታል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J