ለምክክሩ ሀገራዊ እሴቶችን እንደመሳሪያ መጠቀም እንደሚገባ ተገለጸ።

0
23

ባሕር ዳር: ነሐሤ 05/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ቀደም ሲል የነበሩ የመተሳሰብ፣ አብሮ የመኖር፣ የመተጋገዝ፣ የመተባበርና ሌሎች ሀገራዊ እሴቶችን ለሀገራዊ ምክክሩ እንደመሳሪያ መጠቀም እንደሚገባ የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ገልጿል።

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ ቀደም ሲል የነበሩና ሀገራዊ እሴቶችን ለሀገራዊ ምክክሩ በመሳሪነት መጠቀሙ ተገቢ መሆኑን አስምረዋል።

ሆኖም ግን እነዚህን እሴቶች ብቻ እያዜሙ ከመቀጠል የእሴቶቹ ተግዳሮቶች ምን እንደሆኑ፣ የት ላይ ጥፋት እንዳጋጠማቸው መመርመር እንደሚገባ ጠቁመዋል። ጥፋቱ በጣም ከፍተኛ መሆኑን ግን ሁሉም ሰው ልብ ሊለው እንደሚገባም ተናግረዋል።

ኢትዮጵያዊነት በሁሉም አካባቢ እኩል ይዘመራል ወይ? ምንድነው ችግር ያጋጠመው? ለምንድን ነው እንደዚህ አይነት አጀንዳዎች አንዳንድ ቦታ ላይ ጎልተው ሌሎቹ ጋር የሚኮስሱት? የዚህስ ምክንያት ምንድን ነው? ጥፋቱስ የት ጋ ነው? የሚሉትን ጉዳዮች ማጥናት እንደሚገባ አስገንዝበዋል። ዘገባው የኢፕድ ነው

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን‼
ከእኛ ጋር ስለኾኑ እናመሰግናለን‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/