ለህልውና ዘመቻው የድርሻቸውን እንደሚወጡ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሚሠሩ የመንግሥት ሠራተኞች አስታወቁ፡፡

0
41

ለህልውና ዘመቻው የድርሻቸውን እንደሚወጡ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሚሠሩ የመንግሥት ሠራተኞች አስታወቁ፡፡

ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 29/2013 ዓ.ም (አሚኮ) አቶ ይርጋለም አያሌው በኢትዮጵያ ልማት ባንክ ዋናው መስሪያ ቤት ሠራተኛ ናቸው፡፡ የህልውና ዘመቻውን ለማገዝ የመሥሪያ ቤቱን ሠራተኞች በማስተባበር 70 ሺህ ብር ማበርከታቸውን ነግረውናል፡፡ አቶ ይርጋለም አሸባሪው የትህነግ ቡድን ኢትዮጵያን እንደ ሀገር እንዳትቀጥል አቅዶ እየተንቀሳቀሰ መኾኑን ጠቅሰዋል፡፡ ይህንን አሸባሪ ቡድን ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ለመደምሰስ አንድነት እና ድጋፍ ያስፈልጋል ይላሉ፡፡ አቶ ይርጋለም የወር ደሞዛቸው ከመሥጠት በተጨማሪ ኀላፊነታቸውን ለመወጣት እና አጋርነታቸውን ለማሳየት አስበው ድጋፉን ማሰባሰባቸውን ነግረውናል፡፡

የትህነግ ሽብርተኛ ቡድን ኢትዮጵያን ለማፍረስ ቢጥርም አይሳካለትም የሚሉት አቶ ይርጋለም የተሰበሰበው ገንዘብ ጥቂት ቢሆንም “ጋን በጠጠር ይደገፋል” እንዲሉ ለእነሱ አብሮነታቸውን እንደሚያሳይላቸው ገልጸዋል፡፡

የህልውና ዘመቻውን በገንዘብ እና በቁሳቁስ ከመደገፍ ባሻገር በግንባር ለመሰለፍ እቅድ እንዳላቸውም ተናግረዋል፡፡ ኢትዮጵያ ከሌለች በሰላም መኖር እና ወጥቶ መግባት እንደማይቻል በመገንዘብ ሁሉም እንደ አቅሙ የህልውና ዘመቻውን እንዲያግዝ አሳስበዋል፡፡

አቶ አንማው ገዳሙም የዚሁ መስሪያ ቤት ሠራተኛ ናቸው፡፡ አቶ አንማው ሽብርተኛው የትህነግ ቡድን በአማራ ብሎም በኢትዮጵያ ህልውና ላይ ያነጣጠረ ዘመቻ መክፈቱን ተከትሎ የበኩላቸውን እያደረጉ መኾኑን ነግረውናል፡፡

የአማራ ክልል የህልውና ዘመቻውን ለመመከት የክተት ጥሪ ማቅረቡ ይታወሳል፤ይህን የክተት ጥሪ ተከትሎ በርካታ ወጣቶች ወደ ዘመቻው እየተቀላቀሉ በመኾኑ በምግብ እና በቁሳቁስ ለማገዝ አስበው ማድረጋቸውን አቶ አንማው ገልጸዋል፡፡

የሀገርን ህልውና ለመጠበቅ የመንግሥት ሠራተኞች ተሰባስበው ያደረጉት ጥቂት ቢኾንም በማንኛውም ጊዜ መደጋገፍ እና መረዳዳት ለውጤት እንደሚያበቃ ለማሳየት የተደረገ እንደኾ ነው ያስረዱት፡፡ ጓደኞቻቸውን በማስተባበር 70 ሺህ ብር ገቢ ማድረጋቸውን የተናገሩት አቶ አንማው በቀጣይም የሚጠበቅባቸውን ማንኛውንም መስዋእትነት ለመክፈል መዘጋጀታቸውን ጠቁመዋል፡፡ “ሀገር እንትቀጥል የሁሉንም ድጋፍ ትሻለች” የሚሉት አቶ አንማው ማንኛውም ሰው የድርሻውን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ዘጋቢ፡- ትርንጎ ይፍሩ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m