ሀገር አቀፍ የትምህርት ብርሃን ምዘና መርኃ ግብር በይፋ ተጀመረ፡፡

0
84
ሀገር አቀፍ የትምህርት ብርሃን ምዘና መርኃ ግብር በይፋ ተጀመረ፡፡
ባሕር ዳር፡ መጋቢት 22/2013 ዓ.ም (አብመድ) የትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ብርሀን ምዘና የማስጀመሪያ መርኃግብር ላይ የተገኙት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን እንዳሉት የምዘናው ሥርዓቱ መደበኛ ባልሆኑ መንገዶች እውቀትን ያገኙ ዜጎችን በማነቃቃት ሌሎች ዜጎችም ወደ ትምህርት ቤት እንዲመጡ እና መደበኛ እውቀት እንዲያገኙ ያስችላል፡፡
“የትምህርት ብርሀን ምዘና የሀገራችንን የመማር ምጣኔ የሚያሳድግ በመሆኑ ሰው ተኮር የሆኑ ሥራዎችን በመሥራት የተማረ የሰው ኃይልን የማፍራት ተልዕኳችንን መወጣት አለብን” ብለዋል። ሕዝቡም ይህንን እድል እንዲጠቀምበት ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የትምህርት ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩሪያ (ዶ.ር) የትምህርት ብርሀን ምዘና የትምህርት ዘርፉ አንዱ የለውጥ አካል መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በተለያዩ የሙያ ዘርፍ ላይ ያሉ ማንበብ ፣ መፃፍ እና ማስላት የሚችሉ ነገር ግን ያልተመዘኑ እና እውቅና ያላገኙ ዜጎች ተመዝነው እውቅና እንዲያገኙ የሚያደርግ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
ትምህርትን በመስጠት የሃይማኖት ተቋማት ከፍተኛ ሥራዎችን ሲሠሩ መቆየታቸውን እና በዚህም ማንበብ ፣ መፃፍ እና ማስላት የሚችሉ ዜጎች መፈጠራቸውን ሚኒስትሩ ተናግረዋል።
ንቅናቄው ቀጣይነት ያለው እና ሁሉም ማንበብ እና መፃፍ የሚችል ዜጋ በዚህ የምዘና ሥርዓት በማለፍ በተሰማሩበት የሙያ መስክ ውጤታማ እንዲሆኑ የሚያስችል መሆኑን እንደገለጹ ከትምህርት ሚኒስቴር የተገኘ መረጃ ያመላክታል።
የትምህርት ብርሀን ምዘና ማንበብ ፣ መፃፍ እና ማስላት የሚችሉ ዜጎችን እውቅና የሚሰጥ የምዘና ሥርዓት ነው።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here