ሀገራዊ ምክክሩ ውጤታማ እንዲኾን ወጣቶች የነቃ ተሳትፎ ሊያደርጉ እንደሚገባ ተገለጸ።

0
41

ደብረ ማርቆስ: የካቲት 10/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ሀገራዊ ምክክሩ ውጤታማ እንዲኾን ወጣቶች የነቃ ተሳትፎ ሊያደርጉ እንደሚገባ ለአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን (አሚኮ) አስተያየታቸውን የሰጡ የደብረ ማርቆስ ከተማ ነዋሪ ወጣቶች ተናግረዋል፡፡

በሀገር አቀፍ ደረጃ ሊካሄድ ለታሰበው ምክክር ስኬታማነት የድርሻቸውን ለመወጣት ዝግጁ መኾናቸውንም ወጣቶቹ አረጋግጠዋል፡፡

ወጣት መላክ ኃይሉ እንደገለጸው ሀገራዊ የምክክር መድረኩ ባለፉት 27 ዓመታት በነበረው የብሔር ፖለቲካ ምክንያት የተፈጠሩ ችግሮችን ለማስወገድ ያግዛል። እስከዛሬ የቆዩና ለልዩነት ምክንያት የኾኑ ችግሮችን ነቅሶ በማውጣትና ሐሳቦች በነጻነት እንዲንሸራሸሩ በማድረግ ፍትሐዊ የውይይት መድረክ እንዲፈጠር ማስቻል እንደሚገባም ጠቁሟል።

ሀገራዊ ምክክሩ ልዩነቶችን በመፍታት ወደ አንድነት የማምጣት ዕድል ይፈጥራል ያለው ደግሞ ወጣት መስፍን ከበደ ነው፡፡ የሚቋቋመው ኮሚሽንም ከወገንተኝነት በጸዳ መልኩ ሀገሪቷን ሊያገለግል በሚችል ቁመና መገኘት እንዳለበት አመላክቷል።

በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የሥነ ዜጋና ሥነ ምግባር መምህር ረዳት ፕሮፌሰር ገናነው ጀምበሩ ሀገራዊ የምክክር መድረኩ በችግሮች ዙሪያ ተነጋግሮ መፍትሔ ማምጣትና በሂደቱ የሚገኙ ልምድና ተሞክሮዎችን ለተተኪው ትውልድ የምናስተላልፍበት ነው ብለዋል፡፡ ለተግባራዊነቱም የወጣቶች ተሳትፎ ወሳኝ መኾኑን ነው ያስገነዘቡት፡፡

በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የውኃ ምሕንድስና መምህር ዋሴ ደሴ ሀገራዊ የምክክር መድረክ መካሄዱ በሀገሪቱ ዘላቂ ሰላም ከማስፈንና የወጣቶችን የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ጥያቄዎች ከመመለስ አኳያ ትልቅ ሚና እንዳለውም ተናግረዋል። የቆዩ ቁርሾዎችንና አለመግባባቶችን በመቅረፍ ፍትሐዊ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ሀገራዊ ምክክሩ ፋይዳው የጎላ መሆኑን መምህር ዋሴ አመላክተዋል።

ለሀገራዊ ምክክሩ ስኬታማነትም ኹሉም የየድርሻውን ማበርከት እንዳለበትም አስተያየት ሰጪዎቹ ተናግረዋል፡፡

ዘጋቢ፡- መልሰው ቸርነት- ከደብረ ማርቆስ

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/